ዜና ፌ.ቤ.ኮ
Back
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በጋራ የመስክ ሥራ ጉብኝት አካሄዱ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃለፊ ሚኒስትር እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አለምጽሐይ ጳውሎስ ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ጋር በጋራ በዛሬው እለት የኮርፖሬሽኑ ውጤታማ የሥራ እንቅስቃሴን በመስክ ሥራ ጉብኝት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴን ጨምሮ ኮርፖሬሽኑ በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን ማጠናነቀቅ ስለቻለበት የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓቱን በተመለከተም ለክብርት ሚኒስትሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከብርት ሚኒስትሯ በዋናው መ/ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መስረት አድርጎ ኮርፖሬሽኑ እያቀረበ ያለውን አገልግሎትና የዲጂታላይዜሽን አሰራር ሥርዓት ዝርጋታ ያለበት ደረጃንም ተመልክተዋል፡፡
በተመሳሳይ ኮርፖሬሽኑ በአጭር ግዜ ገንብቶ ለአገልግሎት ያበቃቸውን ዘመናዊ ሚክስድ አፓርትምንት ሕንጻዎችን የተመለከቱ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ለውጥና የተቋም ግንባታ ያለበት ደረጃ በጣም ጥሩ እንደሆነ ከብርት ሚኒስትሯ የጠቆሙ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኛ በተገኘው ስኬት ሳይዘናጋ ለላቀ ለውጥና ውጤት እንዲተጋም አበረታተዋል ፡፡
በጉብኝቱ የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አበላትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡