ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማሽን ተከላ ሥራን ለማከናወን የሚያስችለውን የግንባታ ፕሮጀከት አስጀመረ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋለውን የግብዓት ዓቅርቦት እጥረትን የሚያቃሉ የኮንክሪት ውሕድ እና ብሎኬት ማምረቻ ማሽን ተካላ ለማከናወን የግንባታ ፕሮጀክት ሥራን አስጀምሯል፡፡

የፕጀክቱን ግንባታ ሒደት እና ያለበትን ደረጃ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት ጎብኝተዋል፡፡

የማሽን ተከላ ለማከናወን የግንባታ ፕሮጀክቱ መጀመርን አስመልክቶ የኮርፖሬኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከሉ የማሽን ተከላው ሲጠናቀቅ ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውናቸው ሰፋፊ የቤት ልማት ፕሮግራሞች አስተማማኝ የግብዓት አቅርቦት ከመፍጠሩም ባሻገር ለሌሎች በግንባታው ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን በማቅረብ የቤት ልማት ዘርፉን እድገት ለማሳላጥ ኮርፖሬሽኑ እንዳቀደ ነው የገለጹት፡፡

ማዕከሉ በ3 ነጥብ 2 ሄክታር ቦታ ስፋት ላይ ያረፈ ግዙፍ የግንባታ ግብዓት ማምረቻም ማዕከል መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኮንክሪት ባቺንግ ፕላንት ማሽን ተከላ ሲጠናቀቅ በቀን ከ2 ሺህ 400 በላይ ሜትር ኩዩቢክ የኮንክሪት ውህድ የማምረት ዓቅም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የብሎኬት ማምረቻ ማሽኑም በቀን የተለያዩ መጠን ያላቸው ከ60 ሺህ በላይ ብሎኬቶችን የማምረት ዓቅም እንዳለውም ገልጸዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

የኮንክሪት ውህድ እና ብሎኬት ማምረቻው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከ 4 ቢሊየን ብር በላይ ኮርፖሬሽኑ በዓመት ገቢ ማግኘት እንደሚችልም አመላክተዋል፡፡

የጥሬ እቃ አቅርቦትን ጨምሮ የምርት ጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርከሪዎችን የማዘጋጀት ሥራው እንደተጠናቀቀም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

ማእከሉ በሙሉ እቅሙ ወደ ምርት ሲገባ የኮንስትራክሽ ዘርፉን ጥራት ያለው የግንባታ ግብዓት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የኮርፖሬሽኑን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሳደጉም በላይ ኮርፖሬሽኑ ለዘርፉ እድገት የራሱን ሚና ለመጫወት እያደረገ ያለውን ሚና ከፍ እንደሚያደርገውም ያለቸውን እምነት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘርፉን በጋራ ለማሳድግና አብረው ለመስራት በተስማሙት መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ለፕሮጀክት ማእከሉ፣ የግንባታ ቦታ ለኮርፖሬሽኑ ማቅረቡም ተገልጿል፡፡


ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተመራ የልዑካን ቡድን በእንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አካሄደ

በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተመራ የልዑካን ቡድን በእንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አካሄደ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ገቢውን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ አስታወቀ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ገቢውን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ አስታወቀ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአምስተኛ ጊዜ ደም ለገሱ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአምስተኛ ጊዜ ደም ለገሱ

የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች