ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች የኮርፖሬሽኑን የግንባታ ፕሮጀክቶች ጎበኙ

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች የሶማሌ ተራን እና በገርጂ ሳይት እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የኮንክሪት ውሕድና ብሎኬት ማምረቻ ማዕከልን ግንቦት 7/2016 ዓ.ም ጎበኝተዋል።

ሁለቱ ተቋማት በጋራ አብረው መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮችም ውይይት የተደረገ ሲሆን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያገኘውን ልምድና ተሞክሮ ለኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አካፍሏል፡፡

ከፍተኛ አመራሮቹ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የአልሙኒየም ፎርምወርክ የግንባታ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በ18 ወራት ገንብቶ ያጠናቀቃቸዉን የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር እና በፍጥነት በመጠናቀቅ ላይ ያለዉን ባለ 27 ወለል የሱማሌ ተራ ሳይቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ግብዓትን ለገበያ ጭምር እያቀርበ ያለውን እና እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎችን የተገጠመለትን የግብዓት ማምረቻ ፋብሪካ በጥራትና በብዛት የአርማታ ዉህድና የብሎኬት ማቅረብ በሚያስችለው አግባብ እንደተደራጀ አመራሮቹ መታዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዲዛይን፣ በግንባታ ቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ ረገድ ፣ በመሠረተ ልማት እና በአፎርድብል ሀውሲንግ ዙሪያ የልምድ ልውውጥና ምክክርም ሁለቱ ተቋማት አድርገዋል፡፡

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ሀቢብ ቁምቢ እንተናገሩት በአልሙኒየም ፍሬም ወርክ ቴክኖሎጂ የተገነቡት ዘመናዊ ቤቶች ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክትን እንዴት እንደሚመራ እና በተያዘለት ጊዜ ገደብ ፣ ጥራትና በጀት ከማጠናቀቅ አኳያ ያለውን ከፍተኛ ልምድ ወደ ተቋማቸው ወስደው ተግባራዊ ለማድረግ ከኮርፖሬሽኑ ልምድ እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡

በአማካሪ፣ በኮንትራክተር እና በአሰሪ መካካል በተቀናጀ መልኩ በመስራት ከዚህ በፊት አሮጌ ቤቶችን ብቻ ከማከራየት ወጥቶ አዳዲስ ቤቶችን በመገንባት የቤት እጥረትን ለመቅረፍ የሚያደርገውን ጥረት ልምድ የቀሰምንበት በመሆኑ ወደተቋማችን ወስደን የምንተገብራቸው ይሆናል ብለዋል፡፡

አክለውም ሥራችን ተቀራራቢ በመሆኑ በምንችለው መንገድ ሁሉ ተጋግዘን ለፐብሊክ ሴክተሩ የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሪፎርሙ ያገኛቸውን ልምዶችና ስኬቶች እንዲሰፉ ከአቻ የፌዴራል ተቋማትና ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ሲሆን በቅርቡ የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ደርጅት በባህርዳር ከተማ ላስገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር በብቃት የማከር አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል፡፡


ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ከተሰማሩ የጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተደረገ

በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ከተሰማሩ የጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተደረገ

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አደረገ

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን አመሰገነ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን አመሰገነ

የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች