ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

Back

ኮርፖሬሽኑ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

በ2015 በጀት ዓመት በ9 ወራት ውስጥ የታየው የላቀ የእቅድ አፈጻጸም የኮርፖሬሽኑ ስኬታማ የለውጥ ሒደት አስተማማኝ ደረጃ መድረሱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ በግምገማ መድረኩ ተመላክቷል፡፡

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በተመራው በዚህ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቤት አስተዳደር ዘርፍ፣በቤት ልማት ዘርፍ፣በኮንስትራክሽን ግብዓት ዓቅርቦት ዘርፍ፣ በአገልግሎት ዘርፍ እና ስትራቴጅክ የስራ ክፍሎች በኩል በ9 ወራት ውስጥ የተከናወኑ አንኳር የሥራ ክንውኖችን ገምግሟል፡፡

በግምገማውም በገቢ እድገት ረገድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ ጊቢ መገኘቱ በኮርፖሬሽኑ ታሪክ በተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ገቢ አንጻር ሲታይ ከፍተኛ መሆኑ ተገምግሟል፡፡ ለዓብነት እንኳ ከሦስት ዓማታት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 4 እጥፍ የሚጠጋ ብልጫ እንደሚሳይ ነው የተገለጸው፡፡ የገቢ አማራጮች መስፋትና ተቋሙ ያለውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ መቻሉ ለገቢ እድገቱ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደነበራቸውም ተጠቅሷል፡፡

አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ ሀብትም አሁን ላይ ከ260 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑ እንደታወቀም ነው በግምገማው የተመላከተው፡፡

ከተለያዩ ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት የተደረገው ስምምነት ፍሬያማ እየሆነ መምጣቱም ነው የተገለጸው፡፡

የበላይ አመራሩ ሥራዎች በየጊዜው ወጥ በሆነ መልኩ እየገመገመ አቅጣጫ እየሰጠ መሆኑ አሁን ለተገኘው አስተማማኝ ውጤት ምክንያት በመሆኑ ይኸው ተጠንክሮ እንደሚቀጥልም አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዲጂታላይዜሽን ሥርዓት ትግበራው፣ የአቅም ግንባታ ሥራዎቸው፣ በአመራሩና በሠራተኛው መካከል ያለው የተግባርና የአመለካከት አንድነት ማስቀጠል መቻሉ በጥንካሬ ተግምግሟል፡፡

የኮርፖሬሽኑን ሕንጻዎች ደህንነት ለማስጠበቅ ተገቢውን ጥገናና እድሳት ከመሰጠቱም ባሻገር ለመንግስት ተቋማት ቢሮዎችን በማሰዋብ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት መቻሉም በጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እተከናወኑ ያሉ የሪኖቬሽን ስራዎች አፈጻጸምም በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የሚያስችል እንደሆነም ተገምግሟል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ያለው ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ እንዲሁም ንጹህ የኦዲት አስተያየት ያለው የፋይናስ ሥርዓት እንዲኖር እየተጠናቀቁ ያሉ ሥራዎችን ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችል አቅጣጫም ተሰጥቷል፡፡

ኮንስትራክሽን ግብዓት የማምረቻ መሪሳያዎች ተከላ ለማጠናቀቅ ተጨማረ የአሰራር አቅጣጫ ተቀምጦ አሁን ያለውን የኮርፖሬሽኑን ስኬትና ተስፋ ላይ ያተኮረው ግምገማን አጠናቋል፡፡


ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተመራ የልዑካን ቡድን በእንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አካሄደ

በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተመራ የልዑካን ቡድን በእንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አካሄደ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ገቢውን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ አስታወቀ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ገቢውን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ አስታወቀ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአምስተኛ ጊዜ ደም ለገሱ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአምስተኛ ጊዜ ደም ለገሱ

የፌ.ቤ.ኮ ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች