
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ
የቅርንጫፍ ሁለት ጽ/ቤቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ በወረዳ 04
ልዩ ስሙ ቄራ ሰነዶች ማረጋገጫ አካባቢ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 0115-58-42-61/0115-15-45-49
የቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት

መልዕክት
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክት
አዲሱ የለውጥ አመራር ባለፉት አራት ዓመታት ሀገራዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ ተቋሙን ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ሪፎርም አቅዶ በመተግበር በሁሉም ዘርፎች የሚያበረታታና ተስፋ የሚሰጥ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡
በቅርንጫፉ የሰው ሃይል ብዛትና ስብጥር በቁጥር

በቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር
- የውል እድሳት አገልግሎት
- ቤት ማስረከብ
- ለተለያዩ አገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
- በደንበኞጭ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መፍታት
- የንግድ ቤት ዓመታዊ ውል እድሳት
- የመኖሪያ ቤት ቅያሬ ውል መፈጸም
የውል እድሳት አገልግሎት ለማግኘት
- መጨረሻ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ
- ቤቱ መኖርያ ከሆነ በቤት ቁጥር የወጣና የታደሰ መታወቅያ
- ተከራይ ያገባ/ች ከሆነ/ች ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት በማቅረብ የትዳር አጋርን ማስመዝገብ
- ውሉን እስከሚያድሱበት ቀን ድረስ የተጠቀሙበትን የመብራትና የውሃ ክፍያ የተፈፀመበትን መረጃ ኮፒ ማቅረብ
ከውል እድሳት ውጭ የሆኑ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ከኮርፖሬሽኑ የዜጎች ቻርተር ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤
የሥራ ቦታን የማሻሻል ሥራዎች
- በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የስራ ቦታ ማሻሻያ ስራዎች ከተሰሩ የሪፎርም ስራዎች መሃከል ቀደም ሲል ከነበረበት ቢሮ አሁን እየተገለገለበት ያለው በቄራ አካባቢ የሚገኘውን የቢሮ ሪኖቬሽን እና የምድረ-ጊቢ ስራዎችን ተሰርተዋል፤
- የሰራተኞች እና ለአመራሮች ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር የስራ ተነሳሽነት እንዲጨምር ተደርጓል፤
- ለደንበኞች በቂ የመኪና ማቆሚያ እና አገልግሎት ማግኛ ስፍራን ማመቻቸት ተችሏል፤
- በአጠቃላይ ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር ለሌሎችም ሞዴል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማድረግ ተችሏል፡፡
አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የተሰሩ ስራዎች
- በቅርንጫፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትልልቅ የጥገና ስራዎችን ጨምሮ ለምሳሌ የአፓርታማ ዕድሳት፣
- በፊት በኮንትራክተር ይሰራ የነበረው የአፓርትመንቶች የቴራስ ኮንክሪት ስራዎች እና ሌሎች የጥገናና እድሳት ስራዎች ማከናወን፤
- በተሻለ ፍጥነት፣ጥራት እና ወጭ በመቀነስ እንዲከናወኑ ለማድረግ ከፍተኛ ማሻሻያ በማድረግ፤
- ውል እድሳትን ኮምፒዩተራይዝድ በማድረግ እና አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ መስጠት መቻሉ፤
- ለደንበኞች ጥያቄ ፈጣን ምላሽ በመስጠት እና የኪራይ ክፍያን በባንክ በማድግ አገልግሎቱን ማሻሻል ተችሏል፤
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት ዝርጋታ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች
- በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የመዝገብ ቤት መረጃ አያያዝ ወደ ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ መሰራቱ፤
- የቤቶችን የተመረጡ መረጃ ስካን በማድረግ በሶፍት ኮፒ የማደራጀት እና የመምራት eDMS (document management system) መጠቀም፤
- ውሳኔ ለመስጠት ቀላልና ጊዜ ቆጣቢ ዘዴ የሆነውን eHMS(hose management system) መጠቀም መቻሉ፤
- የውል አፈፃፀምን ለመፈፀም የተሻለና (user friendly) የሆነ፤ ስራን ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ የሚችል BOSS(branch office supporting system) በራሱ በቅርንጫፍ አቅም በማልማት የተቀናጀ አሰራር ለመዘርጋት ተችሏል፡፡
- እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ሶፍት ዶክና (softdoc)፣ ቴሌግራም (telegram) በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ የተደገፈ አማስደገፍ ተችሏል፡፡