ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ

   

      የኮርፖሬሽኑ የቅርንጫፍ አራት ጽ/ቤት በቀድሞ አጠራር ወረዳ 15 ቀበሌ 27

      ልዩ ስሙ ካዛንችስ መብራት ኃይል አጠገብ ይገኛል፡፡

      ስልክ ቁጥር 0115-54-92-50/0115-54-92-52/0115-51-42-22

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት

መልዕክት መልዕክት

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክት

አዲሱ የለውጥ አመራር ባለፉት አራት ዓመታት ሀገራዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ ተቋሙን ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ሪፎርም አቅዶ በመተግበር በሁሉም ዘርፎች የሚያበረታታና ተስፋ የሚሰጥ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

በቅርንጫፉ የሰው ሃይል ብዛትና ስብጥር በቁጥር በቅርንጫፉ የሰው ሃይል ብዛትና ስብጥር በቁጥር

በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር

 1. የውል እድሳት አገልግሎት
 2. ቤት ማስረከብ
 3. ለተለያዩ አገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
 4. በደንበኞጭ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መፍታት
 5. የንግድ ቤት ዓመታዊ ውል እድሳት
 6. የመኖሪያ ቤት ቅያሬ ውል መፈጸም

ተጨማሪ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ

የውል እድሳት አገልግሎት ለማግኘት የውል እድሳት አገልግሎት ለማግኘት

 1. መጨረሻ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ
 2. ቤቱ መኖርያ ከሆነ በቤት ቁጥር የወጣና የታደሰ መታወቅያ
 3. ተከራይ ያገባ/ች ከሆነ/ች ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት በማቅረብ የትዳር አጋርን ማስመዝገብ
 4. ውሉን እስከሚያድሱበት ቀን ድረስ የተጠቀሙበትን የመብራትና የውሃ ክፍያ የተፈፀመበትን መረጃ ኮፒ ማቅረብ

ከውል እድሳት ውጭ የሆኑ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ከኮርፖሬሽኑ የዜጎች ቻርተር ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤

የሥራ ቦታን የማሻሻል ሥራዎች የሥራ ቦታን የማሻሻል ሥራዎች

 • ደንበኞች የሚስተናገዱበት ምቹ ቦታዎችን በማመቻቸት፣ ሠራተኛው ደስተኛ ሆኖ ባለጉዳዩን ተቀብሎ ለማስተናገድ እንዲችል እና ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ምቹ የሥራ ቦታዎችን የመፍጠር::
 • የሰራተኛ አቀማመጥ የሥራ ፍሰትን (Office layout) ተከትሎ እንዲቀመጡ የማድረግ::
 • አገልግሎቱን ከተቀመጠው ስታንዳርድ በታች በአጭር ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
 • የቅርንጫፉን ንብረቶች በአግባቡ የመያዝ እና የሠራተኞች የሥራ ቦታ ንፁህና ሳቢ እንዲሆን ተደርጓል፤
 • ለእድሳት የሚውሉ ግብዓቶች በአይነታቸው በማስቀመጥ እና በቀላሉ ለይቶ መጠቀም እንዲቻል በመደረጉ ብክነት መቀነስ ተችሏል፡፡
 • እጅግ ውብ ማራኪ የሆነ መጋዘን ለመስራት ተችሏል፡፡ ይህም ትልቅ ውጤት ተገኝቶበታል፡፡

አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የተሰሩ ስራዎች አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የተሰሩ ስራዎች

 • ባለፉት አመታት በቅርንጫፉ ውስጥ የተለያዩ የሪፎርም እና የለውጥ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ለረዥም አመታት ሳይታደሱ የቆዩ 32 ህንፃዎች በማደስ ውበታቸውን እና ደህንነታቸውን መመለስ ተችሏል።
 • የአፓርታማ የውሃ ቆጣሪዎችን ከውስጥ ወደ ውጭ እንዲወጣ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ያወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ መቀነስ ችሏል::
 • ባለፈው አመትም ለ335 ቤቶች የህንፃ ዕድሣት ስራዎች ያከናወነ ሲሆን በቀጣይም በተያዘው በጀት መሰረት አስፈላጊውን የጥገና እና እድሳት ስራዎችን ይሠራል፡፡ ይህም ህንፃዎቹን ውበታቸውና የእድሜ ቆይታቸውን ጠብቆ ለማቆየት ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
 • ቤቶቹ ላይ አስፈላጊውን የመስክ ምልከታ በማድረግ የህንፃዎችን የቆይታ ጊዜያቸውን በመገምገም እና በመለየት ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ አስፈላጊውን የጥገናና እድሳት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
 • ቅርንጫፉ የመረጃ አያያዙን በማዘመኑ የፋይል መጥፋትን ችግር፣ የባለጉዳይ መጉላላትን፣ በፋይል ፍለጋ የሚባከነው ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይታይ የነበረውን እንግልት በማስቀረት ውጤታማ ሥራ መስራት ተችሏል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት ዝርጋታ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት ዝርጋታ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች

 • በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን ለሌሎች ቅርንጫፎች ልምድ በማካፈል አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ያረጀ የፋይል አያያዝ ዘዴን በማስወገድ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝን ሥርዓት (EDMS) Electronic Document Management System አገልግሎት ላይ በማዋል እና ተግባራዊ በማድረግ የመረጃ አያያዙን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ ተችሏል፡፡
 • ቅርንጫፉ የተደራጀ የመረጃ አያያዝ እንዲኖረው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለደንበኞች ማቅረብ እንዲችል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

ቅርንጫፉ የሚያስተዳድራቸው ቤቶች በክፍለ ከተማ ቅርንጫፉ የሚያስተዳድራቸው ቤቶች በክፍለ ከተማ

ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን አመሰገነ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን አመሰገነ

የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዘመናዊ ለማድረግ ቴክኖሎጂን የሪፎርሙ መሰረት ማድረግ ይገባናል

የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዘመናዊ ለማድረግ ቴክኖሎጂን የሪፎርሙ መሰረት ማድረግ ይገባናል

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ጎበኙ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ጎበኙ

ይከተሉን ይከተሉን

ፖርታሉን የጎበኙ እና በመጎብኘት ላይ የሚገኙ ፖርታሉን የጎበኙ እና በመጎብኘት ላይ የሚገኙ