ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ

   

          የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቀበሌ በቀድሞ አጠራር 06 ባሁኑ አጠራር 04

          ልዩ ስሙ ከዚራ አካባቢ ይገኛል፡፡

          ስልክ ቁጥር 025 1-11-10-38/025 1-11-12-38

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት

መልዕክት መልዕክት

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክት

አዲሱ የለውጥ አመራር ባለፉት አራት ዓመታት ሀገራዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ ተቋሙን ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ሪፎርም አቅዶ በመተግበር በሁሉም ዘርፎች የሚያበረታታና ተስፋ የሚሰጥ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

በቅርንጫፉ የሰው ሃይል ብዛትና ስብጥር በቁጥር በቅርንጫፉ የሰው ሃይል ብዛትና ስብጥር በቁጥር

በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር

 1. የውል እድሳት አገልግሎት
 2. ቤት ማስረከብ
 3. ለተለያዩ አገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
 4. በደንበኞጭ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መፍታት
 5. የንግድ ቤት ዓመታዊ ውል እድሳት
 6. የመኖሪያ ቤት ቅያሬ ውል መፈጸም

ተጨማሪ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ

የውል እድሳት አገልግሎት ለማግኘት የውል እድሳት አገልግሎት ለማግኘት

 1. መጨረሻ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ
 2. ቤቱ መኖርያ ከሆነ በቤት ቁጥር የወጣና የታደሰ መታወቅያ
 3. ተከራይ ያገባ/ች ከሆነ/ች ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት በማቅረብ የትዳር አጋርን ማስመዝገብ
 4. ውሉን እስከሚያድሱበት ቀን ድረስ የተጠቀሙበትን የመብራትና የውሃ ክፍያ የተፈፀመበትን መረጃ ኮፒ ማቅረብ

ከውል እድሳት ውጭ የሆኑ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ከኮርፖሬሽኑ የዜጎች ቻርተር ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤

የሥራ ቦታን የማሻሻል ሥራዎች የሥራ ቦታን የማሻሻል ሥራዎች

 • የሥራ ቦታን ለሰራተኞችና ለተገልጋይ ደንበኞች ምቹ የስራ አካባቢ እንዲሆን ለማድረግ ተቋሙ በመደበልንና በደንበኞች የወጪ መጋራት ዘዴ በመጠቀም ለረጅም ዓመታት ስንገለገልበት የነበረውን የቅርንጫፉ ጽ/ቤት ቢሮ የግንባትና ዕድሳት ስራ በማከናወን አዲስና ለስራ ምቹ ወደሆነ ግቢ በመቀየር አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ የቅርንጫፉ ደንበኞች የእርካታ ደረጃ እንዲጨምርና ቅሬታ በእጅጉ እንዲቀነስ ማድረግ ተችሏል፡፡
 • የቀድሞው ጽ/ቤት በአቧራ ምክንያት የአገልግሎት አስጣጡን ሥራ አስቸጋሪ የሚያደርገውን የምድረግቢውን 500 ካሬ በኮብል እስቶን ማሰራት፣ የአጥር ከፍታን መጨመርና ቀለም መቀባት እንዲሁም የጽ/ቤቱን ከተንበር መቀየር ሥራ ተሰርቷል፡፡
 • የቅርንጫፉ ዕቃ ግምጃ ቤት በካይዘን አሠራር እንዲደራጅ በማድረግ ቀላል፣ ግልፅ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት አመቺ ተደርጓል፡፡
 • በቅርንጫፉ ውስጥ ሊወገዱ የሚገባቸውን ንብረቶች በኮርፖሬሽኑ መመሪያ እና የአሰራር ሥርዓት መሰረት ቀጣይነት ባለው መንገድ የማስወገድ ስራ በአግባቡ ተከናውኗል።

አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የተሰሩ ስራዎች አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የተሰሩ ስራዎች

 • ቅርንጫፉ ራሱን በሰው ኃይል በማደራጀት የድሬደዋ ከተማ ገጽታ የሆኑ ቤቶችን በመንከባከብና ገጽታቸው ተጠብቆ አስፈላጊውን የእድሳትና የጥገና ሥራ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡
 • ኮርፖሬሽኑ በድሬደዋ ቅርንጫፍ ስር የሚያስተዳድራቸው የመንግስትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ቤቶችና ይዞታዎች ላይ የሚፈጸሙ ህገወጥ ተግባራትን ለማስቆምና ሕጋዊ ሥርዓትን በተከተለ አግባብ እንዲተዳደሩ ለማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፤ የፍትህና የጸጥታ አካላት ጋር በመደበኛ ፕሮግራም ተቀራርቦና ተናቦ በመስራት ህጋዊ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ በማድረግ የኮርፖሬሽኑ ህጋዊ መብትና ዘላቂ ጥቅም እንዲከበር ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ላይ እንገኛለን፡፡
 • በራስ አቅም የቤቶች ቆጠራ በማድረግ የቤቶችን አሁናዊ ሁኔታን በመለየት ውል የሚያድሱና የማያድሱትን፣ክራይ የሚከፍሉና የማይከፍሉ፣ውል ያላቸውና የሌላቸውን፣ ህገወጥ ግንባታን፣ ያለ አገልግሎት ዘርፍና ያለንግድ ፈቃድ የሚነግዱ በመለየት በየፈርጅ ፈርጁ ለማኔጅመንት ኮሚቴ በማቅረብና በማስወሰን የማስተካኪያ እርምጃ ተወስዷል፡፡
 • በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ውዝፍ ክራይ ለመሰብሰብና ውል ለማደስ ተችሏል፡፡ከክራይ ውጭ የነበሩ ቤቶችና ይዞታዎችን በመለየት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ በሦስት ዓመታት ውስጥ 1080 ቤቶችን ለመጠገን ተችሏል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት ዝርጋታ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት ዝርጋታ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች

 • የሚፈለጉ መረጃዎችን በጥቂት ሰዓት በቀላሉ ማግኘት በመቻሉ፡፡
 • የተሰበሰበውን የመስክ መረጃ በማደራጀትና በራስ አቅም የዳታ ቤዝ በማልማት የቤቶችን መረጃ ወደ ሲስተም በማስገባት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ ለቤቶች አስተዳደር ሥራ ምቹ መደላድል መፍጠር ተችሏል፡፡
 • የባንክ የኪራይ ገቢን ዳታ ወደ ሲስተም እንዲያስገቡ ለካርዴክስ ሰራተኞች መረጃ ወቅቱን ጠብቆ መድረስ በመቻሉ የባንክ ሰቴትመንት ሳይጠበቅ የገቢ ሪፖርት በቀላሉ ማግኘት ተችሏል፡፡
 • ቅርንጫፉ የሚያስተዳድራቸውን ቤቶች የቆጠራ ሥራ በማከናወን እንዲሁም በራስ ጥረት ሶፍት ዌር በማልምትና መረጃዎችን በሶፍትና በሀርድ ከፒ አደራጅቶ በመያዝ ለተገልጋይ ደንበኞች የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ አሰራር ሥርዓት መዘርጋት ተችሏል፡፡
 • በራስ አቅም አዲስ ሲስተም በመዘርጋት ዘመናዊ የመረጃ ቋት በማዘጋጀትና መረጃዎችን በማስገባት የውል እድሳትና የክፍያ ሥርዓቱን በ online መፈጸም የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል፡፡

በቅርንጫፉ የሚያስተዳድራቸው ቤቶች በቅርንጫፉ የሚያስተዳድራቸው ቤቶች

ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

የአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጂንሲ እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በቤት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ደረሱ

የአዘርባጃን የቤት ልማት ኤጂንሲ እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በቤት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ደረሱ

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች የኮርፖሬሽኑን የግንባታ ፕሮጀክቶች ጎበኙ

የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች የኮርፖሬሽኑን የግንባታ ፕሮጀክቶች ጎበኙ

የፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄን በመቀላቀል የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄን በመቀላቀል የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ይከተሉን ይከተሉን

ፖርታሉን የጎበኙ እና በመጎብኘት ላይ የሚገኙ ፖርታሉን የጎበኙ እና በመጎብኘት ላይ የሚገኙ