የጥገና አገልግሎት
-
የኮርፖሬሽኑ ተገልጋዮች የጥገና ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። በኮርፖሬሽኑ የሚከናወኑ የቤት ጥገና አይነቶች ሁለት ናቸው። እነዚህም የመከላከልእና ተመላላሽ ጥገናዎች ናቸው። የመከላከልጥገና በኮርፖሬሽኑ የጥገና እቅድ መሰረት የሚከናወን ሲሆን ሁሉም የመንግስት ቤቶች በአምስት አመት ውስጥ ጥገና ይደረግላቸዋል። ሌላው የቤት ጥገና አይነት ተመላላሽ ጥገና ሲሆን በአንጻራዊ ሁኔታ አነስተኛ የጥገና ወጪን የሚጠይቅ ነው።
-
ለሚያስተዳድረው ቅርንጫፍ የሚጠገንላቸውን በደብዳቤ ጥያቄ ያቀርባሉ ወይም ይህን ሊንክ በመጫን የደንበኞች የጥገና አገልግሎት መጠየቂያ እና መከታተያያገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ከቀረበ በኋላ በመመሪያው መሠረት ይስተናገዳሉ፡፡