የቤት ክራይ አሰባሰብ አገልግሎት
ስለ አገልግሎቱ ማብራሪያ
ይህ አገልግሎት ለመኖሪያነት አልያም ለድርጅት አገልግሎት የሚውል የመንግስት ቤት ፈላጊዎች ቤት መስጠት ነው። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ያልሆኑ የመንግስት ቤት ፈላጊዎች ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የመንግስት ቤቶችን ሊጠይቁ ይችላሉ። የተጠየቀው ቤት ለመኖሪያነት ከሆነ ክፍት ቤት መኖሩ ታይቶ ሊሰጥ ይችላል። ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ቤቶች በጨረታ ሽያጭ የሚሰጡ ይሆናል።
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-
- የቤት ኪራይ አገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የተገልጋይ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
- ተገልጋይ ከሚኖርበት ቀበሌ በወቅቱ በስሙ የተመዘገበ የመኖሪያ ቤት የሌለው ስለመሆኑ የሚሰጥ ማስረጃ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
- ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
- የተጠየቀው ቤት ለንግድ አገልግሎት የሚውል ከሆነ የንግድ/ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
ዜና ፌ.ቤ.ኮ
ኮርፖሬሽኑ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማጠቃለያ ምዕራፍ እና የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ ግምገማን አጠናቀቀ
ኮርፖሬሽኑ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የማጠቃለያ ምዕራፍ እና የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ ግምገማን አጠናቀቀ