የቤት ኪራይ አገልግሎት
ስለ አገልግሎቱ ማብራሪያ
ይህ አገልግሎት ለመኖሪያነት አልያም ለድርጅት አገልግሎት የሚውል የመንግስት ቤት ፈላጊዎች ቤት መስጠት ነው። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ያልሆኑ የመንግስት ቤት ፈላጊዎች ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የመንግስት ቤቶችን ሊጠይቁ ይችላሉ። የተጠየቀው ቤት ለመኖሪያነት ከሆነ ክፍት ቤት መኖሩ ታይቶ ሊሰጥ ይችላል። ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ቤቶች በጨረታ ሽያጭ የሚሰጡ ይሆናል።
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-
- የቤት ኪራይ አገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የተገልጋይ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
- ተገልጋይ ከሚኖርበት ቀበሌ በወቅቱ በስሙ የተመዘገበ የመኖሪያ ቤት የሌለው ስለመሆኑ የሚሰጥ ማስረጃ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
- ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
- የተጠየቀው ቤት ለንግድ አገልግሎት የሚውል ከሆነ የንግድ/ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ስካን አድርጎ ማያያዝ፤
ዜና ፌ.ቤ.ኮ
የፌ.ቤ.ኮ ኢ- ሜይል
ተዛማጅ ገጾች
በተደጋጋሚ የተጎበኙ ገጾች
-
በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተመራ የልዑካን ቡድን በእንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አካሄደ
-
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ገቢውን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ አስታወቀ
-
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአምስተኛ ጊዜ ደም ለገሱ
-
ኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሱማሌ ተራ ሳይትን የግንባታ ሒደት ጎበኙ
-
ኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሱማሌ ተራ ሳይትን የግንባታ ሒደት ጎበኙ