
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ
የልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ በወረዳ 08
ልዩ ስሙ ባምቢስ አካባቢ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 115- 51-87-71/115- 58-49-53
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት

መልዕክት
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክት
አዲሱ የለውጥ አመራር ባለፉት አራት ዓመታት ሀገራዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ ተቋሙን ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ሪፎርም አቅዶ በመተግበር በሁሉም ዘርፎች የሚያበረታታና ተስፋ የሚሰጥ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡
በቅርንጫፉ ያለው የሰው ሃይል ብዛትና ስብጥር

በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች
- የውል እድሳት አገልግሎት
- ቤት ማስረከብ
- ለተለያዩ አገልግሎት የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
- በደንበኞጭ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መፍታት
- የንግድ ቤት ዓመታዊ ውል እድሳት
- የመኖሪያ ቤት ቅያሬ ውል መፈጸም
የውል እድሳት አገልግሎት ለማግኘት
- መጨረሻ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ
- ቤቱ መኖርያ ከሆነ በቤት ቁጥር የወጣና የታደሰ መታወቅያ
- ተከራይ ያገባ/ች ከሆነ/ች ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት በማቅረብ የትዳር አጋርን ማስመዝገብ
- ውሉን እስከሚያድሱበት ቀን ድረስ የተጠቀሙበትን የመብራትና የውሃ ክፍያ የተፈፀመበትን መረጃ ኮፒ ማቅረብ
ከውል እድሳት ውጭ የሆኑ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ከኮርፖሬሽኑ የዜጎች ቻርተር ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤
የሥራ ቦታን የማሻሻል ሥራዎች
- የልዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሙሉ በሙሉ ፈርሶ እንደ አዲስ ለአገልግሎት ምቹ ለማድረግ የሪኖቬሽን ስራዎች ተሰርቷል፡፡
- ሌላው ምቹ የስራ ቦታን ከመፍጠር አንፃር በርካታ የማሻሻያ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
- የቅርንጫፉ ቋሚና አላቂ ንብረት አያያዝ ለማዘመን በተሰራው ስራ የንብረት ክምችንና ስርጭትን በዘመናዊ መንገድ የራሱ የሆነ የመቆጣጠሪያ ሲስተም ስራ ላይ ውሏል፡፡
- በዚህም የቢሮ፣የካፍቴሪያ፣የስብሰባ አዳራሽ፣የምድረግቢያዊ ስራ እና የቢሮ እድሳት ስራ ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ ማከናወን ተችሏል፡፡
አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የተሰሩ ስራዎች
- በልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የሪፎርም ማሻሻያ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
- በጽ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ከማዘመን አኳያ በዘመናዊ መንገድ ደንበኞችን በኦንላይን ፎቶ በማንሳት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል፡፡
- የዉል እድሳት ሲከናወን ደንበኞች ያለ ምንም መንገላታት አገልግሎቱን ማግኘት ችለዋል፡፡
- የደንበኞችን መረጃዎችም በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ውጤታማ የሪከርድና ማህደር ስራ ተሰርቷል።
- በዚህም ማህደር ሳይንቀሳቀስ በኦንላይን መረጃዎችን በማየትና በማረጋገጥ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። በሌላ በኩል የቅርንጫፉን የገቢ አሰባሰብ ወደ ከባንክ ሲስተም ጋር በማያያዝ ደንበኞች ባሉበት ሆነው በባንክ ሂሳባቸው ተቀናሽ ሆኖ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት ዝርጋታ በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች
- የደንበኞችን መረጃዎችም በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ውጤታማ የሪከርድና ማህደር ስራ ተሰርቷል፡፡ ማህደር ሳይንቀሳቀስ በኦንላይን መረጃዎችን በማየትና በማረጋገጥ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
- በሌላ በኩል የቅርንጫፉን የገቢ አሰባሰብ ወደ ባንክ ሲስተም በማያያዝ ደንበኞች ባሉበት ሆነው በባንክ ሂሳባቸው ተቀናሽ ሆኖ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
- ሌላው በሪፎርሙ ከተሰሩ ስራዎች ደንበኞችን ግዴታቸውን እንዲወጡ የአጭር መልዕክት ማስተላለፊያ (short code) በመጠቀም በድጅታል መልዕክት መረጃ እንዲደርሳቸው የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡
ቅርንጫፉ የሚያስተዳድራቸው ቤቶች በክፍለ ከተማ