ግቦች
የኮርፖሬሽኑ ዓላማዎች
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር398/2009 አንቀፅ 5 መሰረት ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቤቶችን የመገንባት፣ የማስገንባት፣ የማከራየት፣ የመሸጥ እንዲሁም የመግዛት፣
- የፌደራል መንግስትበባለቤትነት የያዛቸውንቤቶችና ይዞታዎችየማስተዳደር፣የማከራየት፣
- ለፌደራል መንግሥት ቤቶችና ህንፃዎች አስፈላጊውን ጥገናና ዕደሳት በማድረግ የመጠበቅና የመንከባከብ፣
- የፌደራል መንግሥት ንብረት የሆኑት ቤቶችና ይዞታዎችበሕግ አግባብ መመዝገባቸውንና መጠበቃቸውን የማረጋገጥ፣
- የፌደራል መንግሥት ቤቶችን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችል ዘመናዊ የቤት አስተዳደር ሥርዓትን በመዘርጋት ሥራ ላይ የማዋል፣
- በመንግስት ቤቶችና ይዞታዎች ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶችንየመከላከል፣ የመንግስትን ጥቅምየማስከበር እና አስፈላጊ ህጋዊእርምጃዎችን የመውሰድ፣
- መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በመንግስት ወጪ ተሸፍነው ለመንግስት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት የመገንባት፣ የማከራየት እና የማስተዳደር፣
- ለሚያስተዳድራቸው ቤቶችና ይዞታዎችየቤት ኪራይ ተመን ጥናትየማካሄድና ተግባራዊየማድረግ፣
- በሽያጭ እንዲተላለፉበመንግሥት ውሣኔ ውሳኔ የተሰጠባቸውን ቤቶች ዋጋ አተማመን ጥናት የማካሄድ፣ ሲወሰን በውሳኔው መሠረትየመፈፀምናየሽያጭ ገቢየመሰብሰብ፣
- ለአስተዳደር አመቺ ያልሆኑ፤ መልሶ ለማልማት የማያስችሉና ኪራያቸው አነስተኛ የሆኑ ቤቶችንና ይዞታዎችን በመንግስት ውሳኔየማስተላለፍ፣
- ለተወረሱ ቤቶች የቀድሞ ባለንብረቶች በሕጉ መሠረት አበልየመክፈል፣
- ከቤት አስተዳደርና ልማት ጋር የተያያዙ ጥናቶችንበማካሄድበመንግስት ሲፈቀድተግባራዊየማድረግ፣
- ከተቆጣጣሪው ባለስልጣን በሚሰጠው አቅጣጫ ላይ በመመስረት በሀገር ውስጥ ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ እገዛ የሚያደርጉለትን የሰው ሀይል፣ የፋይናንስና የዘመናዊ አስተዳደር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለውን ጥናት በማካሄድ ተግባራዊየማድረግ፣
- ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን የማካሄድዓላማዎች ተሰጥቶታል፡፡
ዜና ፌ.ቤ.ኮ
የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል
ተዛማጅ ገጾች
በተደጋጋሚ የተጎበኙ ገጾች
-
በኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተመራ የልዑካን ቡድን በእንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አካሄደ
-
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ገቢውን ለማሳደግ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሊዲንግ አስታወቀ
-
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአምስተኛ ጊዜ ደም ለገሱ
-
ኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሱማሌ ተራ ሳይትን የግንባታ ሒደት ጎበኙ
-
ኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሱማሌ ተራ ሳይትን የግንባታ ሒደት ጎበኙ