ግቦች ግቦች

የኮርፖሬሽኑ ዓላማዎች

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር398/2009 አንቀፅ 5 መሰረት ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቤቶችን የመገንባት፣ የማስገንባት፣ የማከራየት፣ የመሸጥ እንዲሁም የመግዛት፣
  2. የፌደራል መንግስትበባለቤትነት የያዛቸውንቤቶችና ይዞታዎችየማስተዳደር፣የማከራየት፣
  3. ለፌደራል መንግሥት ቤቶችና ህንፃዎች አስፈላጊውን ጥገናና ዕደሳት በማድረግ የመጠበቅና የመንከባከብ፣
  4. የፌደራል መንግሥት ንብረት የሆኑት ቤቶችና ይዞታዎችበሕግ አግባብ መመዝገባቸውንና መጠበቃቸውን የማረጋገጥ፣
  5. የፌደራል መንግሥት ቤቶችን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችል ዘመናዊ የቤት አስተዳደር ሥርዓትን በመዘርጋት ሥራ ላይ የማዋል፣
  6. በመንግስት ቤቶችና ይዞታዎች ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶችንየመከላከል፣ የመንግስትን ጥቅምየማስከበር እና አስፈላጊ ህጋዊእርምጃዎችን የመውሰድ፣
  7. መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በመንግስት ወጪ ተሸፍነው ለመንግስት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት የመገንባት፣ የማከራየት እና የማስተዳደር፣
  8. ለሚያስተዳድራቸው ቤቶችና ይዞታዎችየቤት ኪራይ ተመን ጥናትየማካሄድና ተግባራዊየማድረግ፣
  9. በሽያጭ እንዲተላለፉበመንግሥት ውሣኔ ውሳኔ የተሰጠባቸውን ቤቶች ዋጋ አተማመን ጥናት የማካሄድ፣ ሲወሰን በውሳኔው መሠረትየመፈፀምናየሽያጭ ገቢየመሰብሰብ፣
  10. ለአስተዳደር አመቺ ያልሆኑ፤ መልሶ ለማልማት የማያስችሉና ኪራያቸው አነስተኛ የሆኑ ቤቶችንና ይዞታዎችን በመንግስት ውሳኔየማስተላለፍ፣
  11. ለተወረሱ ቤቶች የቀድሞ ባለንብረቶች በሕጉ መሠረት አበልየመክፈል፣
  12. ከቤት አስተዳደርና ልማት ጋር የተያያዙ ጥናቶችንበማካሄድበመንግስት ሲፈቀድተግባራዊየማድረግ፣
  13. ከተቆጣጣሪው ባለስልጣን በሚሰጠው አቅጣጫ ላይ በመመስረት በሀገር ውስጥ ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ እገዛ የሚያደርጉለትን የሰው ሀይል፣ የፋይናንስና የዘመናዊ አስተዳደር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለውን ጥናት በማካሄድ ተግባራዊየማድረግ፣
  14. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን የማካሄድዓላማዎች ተሰጥቶታል፡፡

ዜና ፌ.ቤ.ኮ ዜና ፌ.ቤ.ኮ

በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ከተሰማሩ የጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተደረገ

በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ከተሰማሩ የጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተደረገ

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አደረገ

ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን አመሰገነ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን አመሰገነ

የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዘመናዊ ለማድረግ ቴክኖሎጂን የሪፎርሙ መሰረት ማድረግ ይገባናል

የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዘመናዊ ለማድረግ ቴክኖሎጂን የሪፎርሙ መሰረት ማድረግ ይገባናል

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ጎበኙ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ጎበኙ

የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል የፌ.ቤ.ኮ ኢ-ሜይል

ይከተሉን ይከተሉን

ተዛማጅ ገጾች ተዛማጅ ገጾች

በተደጋጋሚ የተጎበኙ ገጾች በተደጋጋሚ የተጎበኙ ገጾች

Back

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ጎበኙ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አገራዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ ባካሄደው ተቋማዊ ሪፎርም በፈጠረው ጠንካራ አቅም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ፣ ማህበራዊ አገልግሎት ለሚስጡ ተቋ ማት እንዲሁም ለአገራዊ ፕሮጀክቶች ተከታታይነት ባለው መልኩ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ለመቀዶኒያ እና ለካንሰር ህሙማን ማዕከልም የቢሮ እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል::

በዚሁ መሠረት ኮርፖሬሽኑ ለወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንም የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን በስሩ ላሉ ወገኖችም የሥራ እድል እንዲመቻችላቸው አድርጓል፡፡

ፋውንዴሽኑ ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተከራየውን ቤት በዝቅተኛ የኪራይ ውል እንዲገለገልበትም ተወስኗል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን በመገኘት በፋውንዴሽኑ ስር ለሚገኙ ወገኖች የምሳ ግብዣም አድርገዋል፡፡

ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በጉበኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ ለትርፍ ያልተቋቋሙና ማህበራዊ አገልግሎት ለሚሰጡ በርካታ ተቋማትና ፋውንዴሽኖች በዝቅተኛ ኪራይ ውል ገብተው አገራዊ እንዲሁም ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተግባራት እያከናወኑ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ለወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንም በዝቅተኛ የኪራይ ውል ዋጋ እየሰጠ ያለውን በጎ ተግባር እንዲቀጥል ኮርፖሬሽኑ መወሰኑን ነው ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የተናገሩት፡፡

በቀጣይም በኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች በሚሰራው ዲዛይን መሰረት የማስፋፊያ ሥራዎች ላይ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን መስራች ወንድም ካሊድ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በቤቱ የሚያገኝበትን በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በመተው ለፋውንዴሽኑ በዝቅተኛ ኪራይ ውል እንዲከራይ በመወሰን የፋውንዴሽኑን ቀጣይነት እንዲረጋገጥ አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በርካታ ድጋፎችን ለማድረግ በገባው ቃል መሰረት ፣ ድጋፉን ኮርፖሬሽኑ ከወዲሁ ማድረግ መጀመሩ ፋውንዴሽኑ እንዲጠናከር የራሱን ሚና እንዳለውም ወንድም ካሊድ ተናግረዋል፡፡

በክቡር ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል መሪነት ኮርፖሬሽኑ እያደረገ ያለውን በጎ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ወንድም ካሊድ ጠይቀዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለበርካታ ማህበራዊ ግልጋሎታቸው ከፍ ላሉ ሀገር በቀል ተቋማትና ፋውንዴሽኖች በዝቅተኛ የኪራይ ውል የመስሪያ ቢሮዎችን እያቀረበ ይገኛል፡፡