ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ    

         የቅርንጫፍ ሶስት ጽ/ቤት ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08

         ልዩ ስሙ ካዛንችስ ቶታል ወረድ ብሎ ይገኛል

         ስልክ ቁጥር 0115-53-55-25/0115-15-77-41

Message of the CEO of the Corporation

The Federal Housing Corporation, the former ‘KBAD’, had a long life and provided services in the government housing administration, especially during the Derg era by participating in house...

         

 1. ለአዲስ ተከራይ የመኖሪያ ቤት በውል ማከራየት
 2. ለአዲስ ተከራይ የንግድ ቤት በውል ማከራየት
 3. ቤት ለተጠቃሚው ማስረከብ፤ (ቤቱ ተጠግኖ ከተጠናቀቀ በኋላ የቤቱን ቁልፍና በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ቆጥሮ ማስረከብ)
 4. የመኖሪያ ቤት ዓመታዊ የውል ዕድሳት
 5. የንግድ ቤት ዓመታዊ ውል እድሳት
 6. የመኖሪያ ቤት ቅያሬ ውል መፈጸም

ተጨማሪ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች ዝርዝር ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ

 1. መጨረሻ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ
 2. ቤቱ መኖርያ ከሆነ በቤት ቁጥር የወጣና የታደሰ መታወቅያ
 3. ተከራይ ያገባ/ች ከሆነ/ች ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት በማቅረብ የትዳር አጋርን ማስመዝገብ
 4. ውሉን እስከሚያድሱበት ቀን ድረስ የተጠቀሙበትን የመብራትና የውሃ ክፍያ የተፈፀመበትን መረጃ ኮፒ ማቅረብ

ከውል እድሳት ውጭ የሆኑ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ከኮርፖሬሽኑ የዜጎች ቻርተር ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤

 • የቅርንጫፉ የስራ አካባቢ ለደንበኞች /ተገልጋዮች/ እና ለሰራተኞች ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ የቢሮ ሪኖቬሽን ስራዎችን ተከናውኗል
 • የቢሮ ውስጥ አደረጃጀትም በአዳዲስ ወንበሮች፤ ጠረጴዛዎች፤ የደንበኞች ማረፊያ ቦታዎቸን፤ የአገልግሎት ማስታወቂያ ቴሌቭዥን
 • የቢሮ ውስጥ አትክልቶችን፣ የግቢ እና የቢሮ አመልካቾች ጽሁፎችን
 • የሰራተኛና የጠረጴዛ የደረት ማንነት ባጆችን
 • የምድረ ግቢውን መጸዳጃ እና አትክልቶችን በማስዋብ የስራው አከበቢ ጽዱ እና ምቹ እንዲሆን ተደርጓል

 • በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተካሄደው የሪፎርም ስራ በተለይም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አሰራርን የተደገፈ የማድረግ::
 • ከውል አፈጻጸም ጋር የተያያዙ 15 ተግባራት ከማንዋል አሰራር ውጪ በኮምፒውተር ሲስተም በመታገዝ ስራውን ጀምሮ እስከ ማጽደቅ ያለው ሥራ በአጭር ደቂቃዎች በማከናወን ከፍተኛ የለውጥ ስራ ተሰርቷል::
 • የገቢ አሰባሰቡን በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጋር በሲስተም በማስተሳሰር ደንበኞች የግል ባንክ አካውንት እንዲከፍቱ በማድረግ ክፍያቸውን በባንክ ስርአት እንዲፈጽሙ ተደርጓል፡፡
 • የቅርንጫፉን የንብረት አያያዝና ስርጭት በፒችትሪ ሲስተም በመመዝገብ የንብረት እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የሚያስችል ስርአት ተዘርግቶ ተግባራዊ ተደርጓል::
 • የቋሚ ንብረት /fixed asset registration system/ ምዝገባ ፤ የእልቂት /depreciation/ ዘዴ ተግባራዊ ተደርጋል፡፡

ተጨማሪ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘምን አኳያ የተሰሩ ስራዎች ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ

 • በቅርንጫፉ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አገልግሎት ማለትም የውል አፈጻጸም e-service እና e-documentation የአሰራር ስርአት::
 • የገቢ አሰባሰብ ከባንክ ጋር የተደረገው የቋሚ ትእዛዝ / standing instruction/ የክፍያ ሲስተም::
 • የንብረት ክምችትና አያያዝ ስርጭት አጠቃላይ የፒችትሪ ሲስተም የእቃ ግምጃ ቤት በስቶር ካይዘን /store kaizen/::
 • ሌሎችም በቢሮ ካይዘንና ቋሚ ንብረት አያያዝ እና የእልቂት ስሌት/fixed asset registration and depreciation/ ስርአት እና::
 • የኢ-ሜል ፤የቴሌግራም፤…ወዘተ. ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርአቶች ተግባራዊ በመደረጋቸው በቅርንጫፉ ውስጥ ከፍተኛ የአሰራር ቅልጥፍናን አስገኝቷል፡፡